AfricaEthiopiaPoliticsSocial

ያለፉት 20 ዓመታት ለአፍሪካ ህጻናት ስቃይ የበዛባቸው እንደነበሩ አንድ ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡

ዶችዌሌ እንደዘገበው በአህጉሪቱ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1995 እስከ 2015 በተለያዩ ሰው ሰራሽ ችግሮች ሳቢያ 5 ሚሊዮን ህጻናት የአምስተኛ ዓመት ልደታቸውን ሳያከብሩ ህይወታቸው አልፏል፡፡

ከሟቾቹ መካከል 3 ሚሊዮን የሚሆኑት እድሜያቸው ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ጨቅላዎች ናቸው፡፡

ጥናቱ እንደሚያሳየው በአፍሪካ ከሚሞቱ ህጻናት መካከል የእርስበርስ ግጭት ሰባት በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ይህም ውጤቱ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ነው የሚገለጸው፡፡

ግጭቶች በሚበራከቱባቸው የአህጉሪቱ ክፍሎች ህጻናት የንጹህ ውሀ እና የጤና አገልግሎት በወቅቱ እንዳያገኙ አንቅፋት በመፍጠር ለህጻናቱ ሞት ትልቅ ድርሻ ነበረው ተብሏል፡፡

በስታንፎርድ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑትና ጥናቱን የመሩት ኤራን ቤንዳቪድ እንዳሉት በአፍሪካ አህጉር ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ በ34 ሀገራት ወደ 15 ሺህ የሚጠጉ ግጭቶች ተቀስቅሰዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button