loading
የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ምክር ቤት የካቢኔ አባላት ሹም ሽር አጸደቀ::

የክልሉ ምክር ቤት ለ 27 የካቢኔ አባላት ሹመት መስጠቱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል ፡፡
የክልሉ የካቢኔ አባላት ሹመት የተከናወነው ያላቸውን የትምህርት ዝግጅትና የስራ ልምድን መሰረት ያደረገ ሲሆን ከተሿሚዎቹ መካከል 96 ከመቶ የሚሆኑት የማስተርስ እና ዶክትሬት ድግሪ ያላቸው አባላት እንደሆኑ ተነግሯል፡፡
አዲስ የተዋቀረው ካቢኔም አሁን በክልሉ እየመጣ ያለውን አንጻራዊ ሰላም ለማስቀጠል እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
በግጭቱ እጃቸው አለበት የተባሉ የክልሉ አመራሮችን ከስልጣን በማውረድ ለህግ እየቀረቡ ሲሆን አሁን የተሾሙት አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትም የሪፎርሙ አካል ናቸው ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *