loading
የአዲስ አበባ ሜዲካልና ቢዝነስ ኮሌጅ እና አትላስ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎቻቸዉን አስመረቁ፡፡

አትላስ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ 153 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከነዚህ ዉስጥ 60 ዎቹ ዴንታል ዶክተር ሲሆኑ ፤ቀሪዎቹ ዴንታል ቴራፒና ቴክኒሻን ናቸዉ፡፡
እነዚህ ተማሪዎች በተለይ የጥርስ ህክምና በጥርስ ሀኪም በመታገዝ በማይሰጥባቸዉ አፋር ጋምቤላና ቤንሻንጉል ክልል በመሰማራት በዘርፉ ያለዉን የህክምና ክፍተት ይሞላሉ ተብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ሜዲካልና ቢዝነስ ኮሌጅ በአዲስ አበባ ድሬደዋና ዝዋይ ካምፓሶቹ 500 ተማሪዎችን ትላንት ያስመረቀ ሲሆን በ14 ዙር አስከዛሬ ያስመረቃቸዉ ተማሪዎች ቁጥርም 50 ሺህ መድረሱን ሰምተናል፡፡ከነዚህ መካከልም ለ10 ሺህ ተማሪዎቹ ነጻ የትምህርት እድል ሰጥቷል፡፡
ከ 5 ተማሪ ላንዱ ነጻ የትምህርት እድል አሰራር ወደፊትም እንደሚቀጥል የኮሌጁ ዲን አቶ ሀብታሙ ገቢሳ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *