loading
የ2010 ዓ/ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የማጠቃለያ ውድድር ዛሬ አዳማ እና ሀዋሳ ላይ ይደረጋል፡፡

አርትስ ስፖርት 28/12/2010
የከፍተኛ ሊጉ ውድድር ሙሉ በሙሉ ባይጠናቀቅም ለአጠቃላይ የውድድሩ ሻምፒዮንነት እና ለደረጃ የሚደረግ ጨዋታን ግን ከማድረግ አያግድም፤ በምድብ ሀ ሁሉም የ30 ሳምንታት መርሀ ግብሮች ቢካሄዱም በምድብ ለ አሁን ቀሪ ያልተካሄዱ ጨዋታዎች ይቀራሉ፡፡
በውድድሩ ከምድብ ሀ የአማራ ክልል ተወካዩ ባህርዳር ከነማ በ65 ነጥቦች ቀዳሚ ሁኖ ሲያጠናቅቅ የትግራዩ ሽረ እንዳስላሴ በ54 ነጥቦች ሁለተኛ ሁኖ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
እስከ የመጨረሻው ሳምንት አጓጊ የነበረው የምድብ ለ ቡድኖች ፉክክር፤ በደቡቡ ተወካይ ደቡብ ፖሊስ የበላይነት ተጠናቋል፤ በውድድሩ ደግሞ 61 ነጥቦችን መሰብሰብ ችሏል፡፡ የጅማው ክለብ ጅማ አባ ቡና በውድድሩ በ59 ነጥብ እና 32 ንፁህ ግቦች ተከታዩን ደረጃ ይዞ አጠናቋል፡፡
በዚህም ባህር ዳር ከነማ እና ደቡብ ፖሊስ ለ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር በቀጥታ ተሳታፊነታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን የአጠቃላይ የውድድር አመቱ አሸናፊ ለመሆን 9፡00 ሲል በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይፋለማሉ፡፡ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዳኛ ብሩክ የማነብርሀን ይመሩታል ተብሏል፡፡
ሽረ እንዳስላሴ እና ጅማ አባ ቡና ደግሞ ሶስተኛው የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊነትን ለማረጋገጥ በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም 9፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡ አሸናፊው ቡድን የውድድሩ ሶስተኛ ሁኖ የሚያጠናቅቅ ይሆናል፡፡
ለደረጃ የሚደረገውን ግጥሚያ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ይመሩታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *