AfricaEthiopiaPoliticsSocial

ቻይና ለአፍሪካ እጄ አይታጠፍም አያለች ነው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ለአፍሪካ ሀገራት የ60 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡
ሺ በድህነት ውስጥ የሚገኙ ሀገሮች የእዳ ስረዛ ይደረግላቸዋልም ብለዋል፡፡ ከ60 ቢሊዮን ዶላሩ ውስጥ 15 ቢሊዮኑ ከወለድ ነጻ ብድር፣ የእዳ ስረዛ እና ቀጥተኛ ድጋፍን ይመለከታል፡፡
ቻይና በአፍሪካ የአየር ንብረትን እና የዱር እንስሳትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ 50 ያህል ፕሮጀክቶችን ለማቋቋም እቅድ እንዳላትም ታውቋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ የቻይናና የአፍሪካ ትብብር ሁለቱንም ወገኖች የሚጠቅምና የሚታይ ለውጥ የሚያመጣ ፣ እነዲሁም አረንጓዴ ኢኮኖሚን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት ብለዋል፡፡
ሺ ይህን ያሉት በቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤውን ለመታደም ቤጂንግ ይገኛሉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button