EthiopiaHealthPoliticsRegionsSocial

በአዲስ አበባ 8 ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች የነጻ ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ነው

አርትስ 1/13/2010

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በድረ ገፁ እንደገለፀው ለጎዳና ተዳዳሪዎችና ለአረጋዊያን ነጻ የህክምና አገልግሎትን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መስጠቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን ተግባር ይበልጥ በማስፋትም ከጳጉሜን 1 እስከ 2 ቀን 2010 ዓ.ም ከሃያት ሜዲካል ኮሌጅና ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒዮም ሜዲካል ኮሌጅ የተውጣጡ ወደ 40 የሚጠጉ የህክምና ባለሙያዎች በ8 የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ማለትም፡-
– በልደታ ተክለሃይማኖት ጤና ጣቢያ
– በየካ ሃያት ወረዳ 13 ጤና ጣቢያ፣
– በቂርቆስ ካዛንችስ ጤና ጣቢያ፣
– በአራዳ አራዳ ጤና ጣቢያ፣
– በጉለሌ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ፣
– በአዲስ ከተማ አዲስ ከተማ ጤና ጣቢያ፣
– በንፋስ ስልክ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ እና
– በኮልፌ ዓለም ባንክ ጤና ጣቢያዎች
ነጻ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የህክምና ባለሙያዎችን አሰማርቷል፡፡ በነጻ የህክምና አገልግሎቱም ለአረጋዊያንና ለህጻናት ትኩረት ይሰጣል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ለማስቀጠል እንዲቻል በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ራሱን የቻለ ማህበር ተቋቁሞ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button