![](http://www.artstv.tv/wp-content/uploads/2018/09/41099235_2614343565456522_5705012390785974272_n.jpg)
ሙጋቤ ከምርጫ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፃቸውን አሰሙ
አርትስ 02/13/2010
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ አወዛጋቢውን የምርጫ ውጤት እንደሚቀበሉት ተናግረዋል፡፡
ከምርጫው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አስያየታቸውን የሰጡት ሙጋቤ አሁን ያለፈው አልፏል:: ፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ አሸናፊ መሆናቸውን መካድ አንችልም፡፡ ነገሮችም በመልካም ሁኔታ መጓዝ ጀምረዋል፡፡ እናም ሁሉም በአንድነት ለሀገሩ መልካም ነገርን ለመስራት መዘጋጀት ነው ያለበት ብለዋል፡፡
ሙጋቤ በምርጫው ዋዜማ በሰጡት መግለጫ ፓርቲያቸውን ዛኑ ፒ ኤፍን ወክለው የቀረቡትን ኤመርሰን ምናንጋግዋን አንደማይመርጡ ተናግረው ነበር፡፡