loading
የ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥቅምት17 እንደሚጀመር ተነገረ

አርትስ ስፖርት 02/01/2011

አዲስ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማደግ ከቻሉት ባህር ዳር ከነማ፤ ደቡብ ፖሊስ እና ሽረ እንዳስላሴ ውጭ ያሉት የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊ ክለቦች በተለያዩ ከተሞች የቅድመ ዝግጅት ጊዜያቸውን እያሳለፉ ይገኛሉ፡፡ ለቡድኖቻቸው የሚበጇቸውን ተጫዋቾች እያስፈረሙ ሲሆን መቀጠል የሌለባቸውን ደግሞ እየሸኙ ነው፡፡
ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየወጡ ባሉ መረጃዎች፤ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ የ2011 ፕሪሚየር ጥቅምት17/2011 እንዲጀመር መወሰኑ ተሰምቷል።
በውድድሩ የአምናው ሻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር ፤ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ኢትዮጵያ ቡና፤ መከላካያ፤ ፋሲል ከነማ፤ ባህር ዳር ከነማ፤ ደደቢት፤ መቐለ፤ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፤ ሽሬ እንዳስላሴ፤ አዳማ ከነማ፤ ሀዋሳ ከነማ፤ ወላይታ ድቻ፤ ሲዳማ ቡና፤ ደቡብ ፖሊስ እና ድሬዳዋ ከነማ ተሳታፊ ናቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *