![](http://www.artstv.tv/wp-content/uploads/2018/09/41543080_2618031565087722_2664370472308703232_n.jpg)
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በድሮን ቴክኖሎጂ የታገዘ የጤና አገልግሎት ሙከራ ጀመረ
አርትስ 02/01/2011
መሰረታዊ የሆኑ መድሃኒቶች፣ የክትባት መድሃኒትና ደምን ለማጓጓዝ በጋራ እየሰራን ሲሆን ዛሬ ሙከራ አድርገናል ብለዋል ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን፡፡
ድሮንውኑ በማንኛውም የአየር ፀባይ የሚሰራ ፣ እስከ 5ኪ.ግ ክብደት መሸከም የሚችል፣ በደርሶ መልስ 300 ኪ.ሜ መሸፈን የሚችልና እስከ 5000 ሜትር ከፍታ የሚነሳ ሲሆን ለዚህም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩርያን በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መ/ቤት ስም አመሰግናሁ ብለዋል ዶ/ር አሚር።