AfricaEthiopiaPoliticsSocial

ለደቡብ ሱዳን ሰላም ኢጋድ የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው ገለጹ ::

አርትስ 03/01/2011
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ለደቡብ ሱዳን ሰላም ኢጋድ የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡
በደቡብ ሱዳን ህዝብ የደረሰውን እንግልት እና ስቃይ በማስታወስ ኢጋድ ከሌሎች ባለድርሻ አካላትጋር በመሆን ለሰላም ሂደቱ ተግባራዊ መሆን ጥረት ማድረጉን ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በኤርትራ እና በኢትዮጵያ እንዲሁም በጅቡቲ እና በኤርትራ መካከል የተፈጠረው የወዳጅነት እና የሰላም ድባብ ለቀጠናው ልማት እና ሰላም አመች ሁኔታን እየፈጠረ መሆኑን ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡
የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ እንደተጠናቀቀ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመሩት የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ፡፡አስታውቋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button