loading
ከ3 ሺህ በላይ ጥቅል የዳታ ኢንተርኔት አገልግሎትን በመሸጥ የተጠረጠረ የድርጅቱ የቴክኒክ ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

አርትስ 7/1/2011 ዓ.ም
የኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳሪክተሩ አቶ አብዱራሂም አህመድ እንደተናገሩት በድርጅቱ ውስጥ በቴክኒክ ሰራተኝነት ሲሰራ የነበረ ሰራተኛ ከፌዴራል ፖሊስና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል ብለዋል።
ግለሰቡ የተሰጠውን ሃለፊነት ወደ ጎን በመተው በህገ ወጥ መንገድ ስራውን ለግል ጥቅም በማዋል በተደጋጋሚ ባደረገው ህገወጥ የጥቅል የዳታና ኢንተርኔት አገልግሎት ሽያጭ ከሶስት ሺህ በላይ ጥቅል አገልግሎት ከ2ሺ በላይ ለሆኑ ደንበኞች በህገወጥ መንገድ በመሸጥ በመጠርጠሩ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *