EthiopiaPoliticsRegionsSocial

ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን በቡራዩ ጥቃት ያደረሱ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ መንግስት በቁርጠኝነት ይሰራል አሉ

አርትስ 08/01/2011
በቡራዩ እና አካባቢው ጥቃቱን ያደረሱ እና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸውን አካላት በህግ ተጠያቂ ለማድረግ መንግስት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የተፈናቀሉ ዜጎችም በአግባቡ እንዲቋቋሙ እንደሚደረግ ምክትል ጠ/ሚሩ አቶ ደመቀ መኮንን ተናግረዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቡራዩ ተፈናቅለው በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተጠለሉ ዜጎችን ጎብኝተው ውይይትም አድርገዋል፡፡
እስከአሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተጠርጣሪዎቹም ባሻገር በጥቃቱ ወቅት መከላከል እየቻሉ ከሃላፊነታቸው የተቆጠቡ የህግ አስከባሪ አካላት ላይም ምርመራ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡
በቡራዩ በደረሰው ጥቃት የዜጎች ሕይወት አልፏል፣ ንብረት ተዘርፏል ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button