loading
ባለስልጣኑ በደመራ ምክንያት አደጋ እንዳይደርስ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል አለ

አርትስ 16/01/2011
የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ለአርትስ ቲ ቪ እንደገለጸዉ ደመራን ሰብሰብ ብሎ በጋራ በመደመር፣ የኤሌክትሪክና የስልክ ገመዶች አለመኖራቸዉን አረጋግጦ በመደመር እና ለደመራ ማቀጣጠያ ነዳጅ ጋዝና ቤንዚል ባለመጠቀም አደጋን መከላከል ይቻላል ብሎናል፡፡
የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ችቦዉ ከቤት ተቀጣጥሎ ሲወጣ እንደ ሶፋ መጋረጃና ምንጣፍን ካሉ ተቀጣጣይ ቁሶች በማራቅ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ፡፡
የደመራዉ ስነስርዓት ሲጠናቀቅም እሳቱ መጥፋቱን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል አቶ ንጋቱ፡፡
አደጋ ከተከሰተ በነጻ የስልክ መስመር 939 እና በ0111555300 በአስቸኳይ አሳዉቁን ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *