loading
‹‹UMBRO›› ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር የትጥቅ አቅርቦት ውል መፈራረሙን አስታወቀ፡፡

‹‹UMBRO›› ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር የትጥቅ አቅርቦት ውል መፈራረሙን አስታወቀ፡፡

 

አምብሮ የተሰኘው የእግር ኳስ ትጥቆች አምራች ኩባንያ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር የትጥቅ አቅርቦት ውል መፈራረሙን በይፋ አስታወቀ።

 

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከጣልያኑ ኤሪያ ጋር ሲሰራ የቆየ ሲሆን ከጣልያኑ ትጥቅ አምራች ጋር ቀሪ ውሉን በማቋረጥ  መቀመጫውን በእንግሊዟ ማንችስተር ከተማ ያደረገው ግዙፍ የትጥቅ አምራች ኩባንያ አምብሮ ጋር የአራት ዓመታት ውል አስሯል።

 

አምብሮ ከዚሀ ቀደም የብራዚል እና እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድኖች እንዲሁም ማንቼስተር ዩናይትድን ለመሳሰሉ ታላላቅ ቡድኖች ምርቱን ያቀረበ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከእንግሊዙ ክለብ ኤቨርተን፣ ዌስትሃም፣ ከጀርመኑ ሻልከ፣ ከኔዘላንዱ ፒ.ኤስ.ቪ እና ሌሎች ክለቦች ጋር እየሰራ ይገኛል።

 

ሶከር ኢትዮጵያ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *