AfricaPolitics

ካቢላ በኖሩበት ቤተ መንግስት በእንግድነት ተጋበዙ፡፡

ካቢላ በኖሩበት ቤተ መንግስት በእንግድነት ተጋበዙ፡፡

የቀድሞው የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ላውረን ካቢላ እሳቸውን ተክተው በቅርቡ ወደ ስልጣን ከመጡት ከፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሽሲኬዲ ጋር ጥምር መንግስት ስለመመስረት ተወያይተዋል ተብሏል፡፡

ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው የቀድሞው እና የአሁኑ ፕሬዝዳንቶች ከሁለቱም ወገን ሌላ ሰው ሳያካትቱ በመጀመሪያ ለብቻው መክረዋል፡፡

ካቢላ እና ሽሲኬዲ ውይይቱን ያደረጉት በሀገሪቱ መንግስት ለመመስረት ጠቅላይ ሚኒስርት ለመሰየም ነው ተብሏል፡፡

ፓርቲያቸው የፓርላማውን ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያላገኘው ፕሬዝዳንት ሽሲኬዲ  እስካሁን ጠቅላይ ሚኒስትር  አልሾሙም፡፡

የፓርላማ መቀመጫውን በብዙ ልዩነት ያሸነፈው የካቢላ ፓርቲ መሆኑ የአሁኑ ውይይት የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ከወዴት እንደሚሆን አመላካች ነው ተብሏል፡፡

የሽሲኬዲ ተቀናቃኝ ሆነው ለምርጫው ቀርበው የነበሩት ማርቲን ፋዩሉ አሸናፊውን ፕሬዝዳንት በካቢላ ተመልምለው ስልጣን ላይ የወጡ ፖለቲከኛ እንጂ ተፎካካሪ አይደሉም ብለው አጥብቀው ተከራክረው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ፋዩሉ እንዲያውም የአፍሪካ ህብረት አዲስ አበባ ላይ ጉባኤውን ሲያካሂድ በኮንጎ በስድስት ወራት ውስጥ ድጋሚ ምርጫ እንዲካሄድ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለህብረቱ እስከመፃፍ ደርሰው ነበር፡፡

መንገሻዓለሙ

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button