loading
የኤፍ ኤ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ዕጣ ድልድል ይፋ ሁኗል

የኤፍ ኤ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ዕጣ ድልድል ይፋ ሁኗል

 

 

ትናንት ምሽት ከተካሄደው የቼልሲ እና ማንችስተር ዩናይትድ የአምስተኛ ዙር ጨዋታ መጠናቀቅን ተከትሎ የኤምሬት ኤፍ ኤ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ የዕጣ ድልድል ይፋ ሁኗል፡፡

 

 

በዕጣ ድልድሉ ማንችስተር ዩናይትድ በፕሪሚየር ሊጉ ጥሩ ግስጋሴ ላይ ከሚገኘው ወልቭስ ጋር ተደልድሏል፤ ጨዋታው ደግሞ በሞሊኒክስ ስታዲየም ይካሄዳል፡፡

 

 

ማንችስተር ሲቲ ደግሞ  ወደ ዌልስ ምድር አቅንቶ ከስዋንሲ ሲቲ የሚፋለም ሲሆን ዋትፎርድ ከ ክሪስታል ፓላስ ጋር ተገናኝቷል፡፡ ሚልወል በሜዳው ብራይተንን ያስተናግዳል፡፡

 

 

የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ከመጋቢት 15- 18/2019 የሚከናወኑ ሲሆን አሸናፊዎቹ ቡድኖች የ750 ሺ ፓውንድ ሽልማት ያገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *