EthiopiaSocial

በኮተቤ አርማታ በመሞላት ላይ ያለ የድልድይ  ግንባታ ተደርምሶ 15 ሶዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

በኮተቤ አርማታ በመሞላት ላይ ያለ የድልድይ  ግንባታ ተደርምሶ 15 ሶዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ልዩ ስሙ ማርያም ቤተክርሲቲያን አጠገብ አርማታ  በመሞላት  ላይ ያለ የድልድይ ግንባታ ተደርምሶ 15 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል

የአዲስ አበባ  እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር  ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሃለፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ለአርትስ ቲቪ እንደገለፁት  ትላንት እረፋድ 4 ሰዓት ላይ አደጋው የደረሰ ሲሆን በዚህም በ 15 ሰዎች ላይ  ከባድ እና ቀላል ጉዳት መድረሱን ተናግረው የሞተ ሰው ግን የለም ብለዋል፡፡

ሃላፊው በመደርመስ አደጋው የተጎዱ እና የተሸፈኑ  ሰዎችን ለማዳን የባለስልጣኑ ሰራተኞች እስከ ሊሊቱ 6 ሰዓት ድረስ ቁፋሮ እያከናወኑ መቆየታቸውን ገልፀው አሁንም ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ነግረውናል፡፡

በተያያዘም መንገዱን በዋናነት የሚያስገነባው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የኮምዮኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሮክተሬት  ዳይሬክተር  አቶ ጡማይ  ወ/ገብርኤል  ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት  አደጋው በምን ምክንያት እንደተከሰተ በማጣራት ላይ መሆናቸውን  ገልፀዋል፡፡

አቶ ጡማይ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ የዋና መንገድ ግንባታ ከተጀመረ አንድ አመት የሞለው መሆኑን አስታውሰው ፤ግንባታውን  በቀጣዩ አመት ለማጠናቀቅ ታስቧል ብለውናል ፡፡

የመንገዱን ግንባታ ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን የሚሰራው ሲሆን የማማከሩን ስራ ደግሞ ዩኒ ኮን የተባለው ድርጅት እንደሚያከናውነው ሰምተናል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button