EthiopiaPolitics

በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሚኖሩ የአገው ማህበረሰብ በህገ መንግስቱ መሰረት በራሳቸው ቋንቋ የመማር እና እኩል ተጠቃሚነታቸው ሊረጋገጥ ይገባል አለ የአገው ብሄራዊ ሸንጎ፡፡

በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የሚኖሩ የአገው ማህበረሰብ በህገ መንግስቱ መሰረት በራሳቸው ቋንቋ የመማር እና እኩል ተጠቃሚነታቸው ሊረጋገጥ ይገባል አለ የአገው ብሄራዊ ሸንጎ፡፡

የአገው ብሄራዊ ሸንጎ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የማህበረሰቡ ማንነት ለዓመታት ሲሸረሸር መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን በመሰረተልማት በኩልም ትኩረት ካላገኙ አከባቢዎች አንዱ ነው ተብሏል፡፡

የአገው ብሄራዊ ሸንጎ ሊቀመንበር  አቶ አላምረው ይርዳው  በቀጣይ በሚካሄደው ሀገራዊ ህዝብና ቤት ቆጠራ ላይ የአገው ማህበረሰብ በትክክለኛው መንገድ ሊቆጠር ይገባል ብለዋል፡፡

በዚህም ማህበረሰቡ በክልል እና በፌዴራል ደረጃ በተገቢውና በተመጣጣኝ መልኩ እንዲወከል ያደርገዋል ነው ያሉት ሊቀ መንበሩ፡፡

በቅርቡ ከማንነት ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ እተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት መንግስት ህዝቡ ከመረጣቸው ኮሚቴዎች እና ከህዝቡ ጋር በመቀራረብ መፍትሄ ሊያበጅ ይገባል ያሉት አቶ አላምረው፤ የአገው ብሄራዊ ሸንጎ ይህንን ዓላማ ከሚደግፉ ፓርቲዎች ጋር በጥምረት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button