loading
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች መመለሳቸው ተገለፀ

በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች መመለሳቸው ተገለፀ

የምዕራብ ወለጋ ዞን  ኮማንድ ፖስት እንዳስታወቀው  በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች ተመልሰው በአሁን ወቅት በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው ተመልሰዋል ብሏል፡፡

በዞኑ በነበረው የፀጥታ ችግር የተዘረፉ 110 ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ 41 ሽጉጦችና 20 የእጅ ቦምቦች እንዲሁም ሌሎች ንብረቶች መመለሳቸውን የኮማንድ ፖስቱ ጽህፈት ቤት አስተባባሪ አቶ ደጀኔ ገብረ ማርያም ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም 326 ኋላ ቀር ጠመንጃዎችና ከ4 ሺህ በላይ ጥይቶች ፣ 50 በርሜል ነዳጅ፣14 የመንግሥትና የግል ተሽከርካሪዎች ፣28 የሞተር ቢስክሌቶችም በተመሳሳይ መመለሳቸውን አቶ ደጀኔ ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የኢዜአ ነው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *