AfricaPolitics

አልበሽር በአሜሪካ ጫና እስረኞችን መፍታት ጀመሩ፡፡

አልበሽር በአሜሪካ ጫና እስረኞችን መፍታት ጀመሩ፡፡

ሱዳን ለወራት በዘለቀው ህዝባዊ አመፅ ተሳትፈዋል ተብለው ከታሰሩት ሰዎች መካከል ከ2 ሺህ 400 በላይ የሚሆኑትን መፍታቷ ተሰምቷል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው  የፕሬዝዳንት  ኦማር አልበሽር አስተዳደር ይህን እርምጃ የወሰደው ከአሜሪካ መንግስት በደረሰበት ጫና ነው፡፡

ሱዳን ከአሜሪካ መንገስት የሽብርተኝነት መዝገብ ስሟ እንዲሰረዝላት ጥረት  በምታደርግበት ወቅት ይህ አጋጣሚ መፈጠሩ ነገሩን የባሰ ውስብስብ አድርጎባታል ነው የተባለው፡፡

ይሁን እንጂ አልበሽር እስረኞችን ቢፈቱም ለተቃውሞ ሰልፈኞቹ በከንቱ አትድከሙ ከስልጣን አልወርድም ብለዋቸዋል፡፡

ወጣቶች ሀገሪቱን ለመረከብ ከፈለጋችሁ ቀድማችሁ ተደራጁ እና ሁሉም ነገር በምርጫ የሚከናወን ይሆናል ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button