loading
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለረዥም ጊዜ ሳይሰበሰብ የቆየ 665 ሚሊዮን ብር ውዝፍ ሂሳብ ሰበሰብኩ አለ፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለረዥም ጊዜ ሳይሰበሰብ የቆየ 665 ሚሊዮን ብር ውዝፍ ሂሳብ ሰበሰብኩ አለ፡፡
አገልግሎቱ ይህንን ያለዉ ያለፉትን የስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ የአገልግሎት አሰጣጥ ከማሻሻል አኳያ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረው፤ በአዲስ አበባ ያለውን የሃይል መቆራረጥ ለማስተካከል በ62 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የኔትወርክ ማሻሻያ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ አፈጻጸሙም 75 በመቶ መድረሱም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
በግማሽ አመቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በስምንት ከተሞች የሃይል ማስተላለፊያ መልሶ ግንብታ እና አቅም የማሳደግ ስራ 61 በመቶ ተጠናቋል ተብሏል፡፡
ባለፈው ታህሳስ ወር ላይ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ የህብረተሰቡን አቅም ያገናዘበ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው ፤ተቋሙ ለግብዓት አቅርቦት ግዢ የሚያወጣውን የዓለም አቀፉን ገበያ ዋጋ መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል፡፡
በግማሽ አመቱ 61 አዳዲስ የገጠር ከተሞች የሃይል ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በቀጣይ 54 ከተሞችን የሃይል ተጠቃሚ ለማድረግ ጥናት ተደርጎ ፋይናንስ የማፈላለግ ስራ እየተሰራ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *