loading
በምስራቃዊ  የኮንጎ ግዛት የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ ተቆጣጥሬያለሁ ሲል የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

በምስራቃዊ  የኮንጎ ግዛት የተከሰተውን የኢቦላ ቫይረስ ተቆጣጥሬያለሁ ሲል የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

በዴሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎ  የኢቦላ ቫይረስ በሰፊው ከተሰራጨባቸው አካባቢዎች የምስራቃዊ ኮንጎ ግዛት ዋነኛው ቢሆንም በዚሁ አካባቢ ያለውን ስርጭት መግታት መቻሉን ነው የሀገሪቱ ጤናጥበቃ ሚኒስቴር ያስታወቀው፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በኒ በተባለውና ቫይረሱ በስፋት ተሰራጭቶበት በነበረው የሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ባለፉት 21 ቀናት አዲስ ህሙማን ያለመመዘገቡን ገልጿል

በሌላ በኩል ቡተምቦና ካትዋ በተባሉ ቦታዎች ባለፉት ሶስት ሳምንታት 74 ህሙማን መመዝገባቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ሲጂቲኤን እንደዘገበው ሀገሪቱ ከቫይረሱ ስርጭት ነፃ ሆናለች የሚለውን ለማወጅ ለ42 ተከታታይ ቀናት አዳዲስ ህሙማን ሳይመዘገቡ መቆየት አለባቸው፡፡

ከህሙማኑ መካከል 528 ህይወታቸው ማለፉም ነው የተነገረው፡፡

በሀገሪቱ ያለው የሰላም ሁኔታ የቫይረስ ስርጭቱን ለመከላከል ሀገሪቱ የምታደረገው እንቅስቃሴ  ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ ይነገራል፡፡

በግዛቱ ተሰራጭቶ በነበረው በዚሁ የኢቦላ ቫይረስ  ከ500 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡ ዘገባው የሲጂቲኤን ነው፡፡

 

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *