loading
ኢትዮጵያዊው እግር ኳስ ተጫዋች ቢኒያም በላይ ወደ ስዊድን አመራ ።

ኢትዮጵያዊው እግር ኳስ ተጫዋች ቢኒያም በላይ ወደ ስዊድን አመራ ።

 

ከስከንደርቡ ጋር ሁለት የተሳኩ ዓመታት ያሳለፈው ኢትዮጵያዊው አማካይ ቢኒያም በላይ የስዊድኑ ክለብ ሴሪያንስካን ተቀላቅሏል።

 

የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ከአልባንያው ቻምፒዮን ጋር ባለፈው ሳምንት የተለያየ ሲሆን በአውሮፓ ሁለተኛ ክለቡ የሆነው ሴሪያንስካን ተቀላቅሏል።

 

የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካይ በዚቬደን ሚሎሶቪች ወደሚሰለጥኑት ሴሪያንስካዎች ማምራቱን ተከትሎ በሶስት የተለያዩ ጊዜያት ለክለቡ ከተጫወተው ዩሱፍ ሳላህ በመቀጠል ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ይሆናል።

 

በ2018 ከስዊድን ሦስተኛ የሊግ እርከን (ዲቪዥን አንድ) በመለያ ጨዋታ ወደ ሁለተኛው እርከን (ሱፐርታን) ያደገው ሴሪያኖስካ ከአንድ ወር በኋላ በሚጀምረው የስዊድን የሊግ ውድድር ላይ ዳገርፎርስን በሜዳው በመግጠም ከ2013 በኋላ ወደ ዋናው ሊግ የመመለስ ፈተናውን ይጀምራል።

 

ምንጭ :- ሶከር ኢትዮጵያ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *