loading
ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ በቁጥጥር ስር ዋለ

ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ በቁጥጥር ስር ዋለ

ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ቀናት በድምሩ 1,506,260 ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ ጅግጅጋ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው ኮንትሮባንድ ኬሚካል፣ ስኳር እና የቁም እንስሳት የሚያካትት ነው፡፡ በዚህ መሰረት በእግር እየተነዱ ከሀገር ሊወጡ የነበሩ ግምታዊ ዋጋቸው 112,500 ብር የሆነ ዘጠኝ በሬዎች የካቲት 16 ቀን 2011 ዓ.ም ሌሊት 7፡00 ጅግጅጋ ውስጥ በሚሊሻና በጉምሩክ አባላት ሲያዙ ተጠርጣው ለጊዜው ማምለጡን ነው የተገለፀው፡፡

በተመሳሳይ ታክስና ቀረጥ ያልተከፈለበት 80 በርሜል ለስፖንጅ ፋብሪካ የሚውል ኬሚካል(HLB polymer polyol) ኮድ3-02857 ሱማ በሆነ ተሸከርካሪ ወደ ሀገር ሊገባ ሲል የካቲት 17/2011 ዓ.ም በፌዴራል ፖሊስና በጉምሩክ አባላት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በወቅቱ የሱፍ ሀሰን መሀመድ አህመድና ከድር አህመድ የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በዛሬው ዕለት እንደዚሁ ከንጋቱ 12፡00 ግምታዊ ዋጋው 500 ሺህ ብር የሆነ 1000 ከርጢት ስኳር በሰሌዳ ቁጥር 04445 ሹማ በሆነ ተሸክርካሪ ወደ ጅግጅጋ ለማስገባት ሲሞከር ጃማ ሀሰን እና አብዲ ጃማ ከተባሉ ተጠርጣዎች ጋር በፌዴራል ፖሊስና በጉምሩክ አባላት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *