loading
ጅማ አባ ጅፋር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከውድድር ታገደ

ጅማ አባ ጅፋር በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከውድድር ታገደ

የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በጅማ አባ ጅፋር እግር ኳስ ክለብ ከየካቲት 29/2011 ዓ/ም ተግባራዊ የሚሆን የማንኛውም አይነት የፌዴሬሽኑ ውድድሮች ላይ ዕገዳ የተላለፈበት የዲሲፕሊን ውሳኔን ተግባራዊ ባለማድረጉ መሆኑን ፌዴሬሽኑ ለአርትስ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የክለቡ ተጨዋች የሆነው አብዱልፈታ ከማል  ከክለቡ ጋር ውል እያለው ከመስከረም ወር 2010 ዓ/ም ጀምሮ ውሉ በክለቡ በመቋረጡ ባቀረበው አቤቱታ የዲሲፕሊን ኮሚቴ ው ተመልክቶ ለአመልካች ያልተከፈለው ደመወዝ ታስቦ በአምስት ቀናት ጊዜ ውስጥ ክለቡ እንዲከፍል በ12/06/2010 በተጻፈ ደብዳቤ ዲሲፕሊን ኮሚቴው ያሳወቀ ቢሆንም ተግባራዊ ሳይደረግ በመቆየቱ በ12/08/2010 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ቀጣይ እርምጃ ክለቡ ላይ እንደሚወስድ ያሳወቀ ቢሆንም ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ሳያደርግ ቆይቷል፡፡

በመሆኑም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ከየካቲት 29/2011 ዓ.ም ጀምሮ ክለቡ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጀው እግር ኳስ ውድድር የታገደ መሆኑን የዲሲፕሊን ኮሚቴው አሳውቆናል ሲል የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ለአርትስ በላከው ዝርዝር የቅጣት መርጃ አድርሷል፡፡

በዚህም አዲስ ውሳኔ እስካልተላለፈ ድረስ፤ ክለቡ በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ የማይካፈል ይሆናል፡፡

 

ጅማ አባ ጅፋር የእግር ኳስ ክለብ የዲሲፕሊን ውሳኔን ተግባራዊ ባለማድረጉ ከየካቲት 29-2011 ጀምሮ ፌዴሬሽኑ ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች መታገዱ ተገለፀ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *