loading
የ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ፡፡

የ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይከናወናሉ፡፡

በሊጉ መርሃግብር ዛሬ ምሽት አራት ያህል ግጥሚያዎች ይደረጋሉ፡፡

ምሽት 4፡45 ላይ በተመሳሳይ ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ የመርሲ ሳይዱ ኤቨርተን ወደ ዌልስ አምርቶ ከካርዲፍ ሲቲ ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡

ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ሀደርስፊልድ ታውን ደግሞ በጆን ስሚዝ ስታዲየም በኑኖ እስፐሪቶ ሳንቶ የሚሰለጥነውን ወልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ያስተናግዳል፡፡

ምሽት 5፡00 ላይ እንዲሁ በተመሳሳይ ሰዓት ሁለት ፍልሚያዎች ሲካሄዱ፤ ክላውድ ፑኤልን ከአሰልጣኝነት ያሰናበተው ሌስተር ሲቲ በአሰልጣኝ ማይክ ስቶዌል እና አዳም ሳድለር እየተመራ ኪንግ ፓወር ላይ ብራይተንን ይገጥማል፡፡

የራፋኤል ቤኒቴዙ ኒውካስትል ዩናይትድ በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በ27ኛው ሳምንት መርሃግብር በቶተንሃም ላይ የ2 ለ 1 ድል ካሳካው በርንሊ ጋር ይጫወታል፡፡

የሊጉ ሌሎች ጨዋታዎች ነገ ሲቀጥሉ አርሰናል ከ ቦርንመዝ፣ ሳውዛምፕተን ከ ፉልሃም፣ ቼልሲ ከ ቶተንሃም፣ ክሪስታል ፓላስ ከ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ሊቨርፑል ከ ዋትፎርድ እና ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስት ሃም ዩናይትድ ጋር ይጫወታሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *