loading
በኮፓ ኢጣሊያ የግማሽ ፍፃሜ ላትሲዮ ከኤስ ሚላን ዛሬ ምሽት ጋር ይገናኛሉ፡፡

በኮፓ ኢጣሊያ የግማሽ ፍፃሜ ላትሲዮ ከኤስ ሚላን ዛሬ ምሽት ጋር ይገናኛሉ፡፡

 

በኮፓ ኢጣሊያ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ግጥሚያ ዛሬ ላትሲዮ እና ኤስ ሚላን በእስታዲዮ ኦሊምፒኮ ምሽት 5፡00 ላይ ይጫወታሉ፡፡

እንግዳው ሚላን የውድድር ዓመቱ ጥሩ ብቃት ላይ የሚገኝ ሲሆን ሮም ላይ በምሽቱ መልካም ውጤት ይዞ ለመምጣት ሰፊ ግምት ተሰጥቶታል፡፡

የጅናሮ ጋቱሶ ቡድን ባለፉት ስምንት ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት ያላስተናገደ ሲሆን ላትሲዮ በአሰልጣኝ ሲሞኔ ኢንዛጊ እየተመራ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈት ደርሶበታል፡፡

ኮለምቢያዊው ተከላካይ ክሪስቲያን ዛፓታ ለሚላን በምሽቱ የማይሰለፍ ተጫዋች ሲሆን ጉዳት ላይ የሚገኘውን ጃክ ቦናቬንቹራን ተቀላቅሏል፡፡

በላትሲዮ በኩል በርካታ ተጫዋቾች ጉዳት ላይ በመገኘታቸው ጨዋታው ያመልጣቸዋል ተብሏል፤ ተከላካዮቹ ሊዊስ ፊሊፔ፣ ባስቶስ፣ ዋላስ እና ጆርዳን ሉካኩ ጉዳት ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

አዲሱ የኤስ ሚላን ፈራሚ ክሪዚስቶፍ ፒያቴክ የምሽቱ ልዩነት ፈጣሪ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *