loading
ሙሀማዱ ቡሀሪ ለሁለተኛ ጊዜ አሸነፉ፡

ሙሀማዱ ቡሀሪ ለሁለተኛ ጊዜ አሸነፉ፡፡

የናይጀሪያ የምርጫ ኮሚሽን ባለፈው ቅዳሜ በሀገሪቱ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከ2015 ጀምሮ በስልጣን ላይ ያሉት ሙሀማዱ ቡሀሪ አሸናፊ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ቡሀሪ የቀድሞውን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የንግድ ሰው አቲኩ አቡበከርን በሰፊ ልዩነት ነው ያሸነፉት፡፡

ይሁን እና የአቲኩ አቡበከር ፒፕልስ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምርጫው ለሳምንት ከመራዘሙ ባሻገር በድምፅ አሰጣጥ ወቅት ወከባ እንደነበር በመግለፅ በውጤቱም ጥርጣሬ እንዳለው  ተናግሯል፡፡

ቡሀሪ በሚቀጥሉት 4 ዓመታት በፕሬዝንትነት ናይጀሪያን ሲመሩ ዋነኛ ስራቸው ሙስናን መወዋጋት እንደሚሆን ከምርጫው በፊት በነበረው የቅስቀሳ ዘመቻ ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

ምርጫውን የታዘቡ አካላት በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ችግር ስለመኖሩ እስካሁን ያሉት ነገር የለም፡፡

መንገሻ ለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *