loading
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ123ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓድዋ ድል በዓል ለየት ባለ መልኩ ለማክበር  ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 123 ጊዜ የሚከበረውን የዓድዋ ድል በዓል ለየት ባለ መልኩ ለማክበር  ዝግጅቴን ጨርሻለሁ አለ ።

 

የከተማ አስተዳደሩ የፕሬስ ሴክረታሪ ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ እና የባህል የኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊው ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በአሉን ለማክበር ስለተዘጋጁት መርሃግብሮች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በወጣው ፕሮግራም መሰረት  ሐሙስ  የካቲት 21 ቀን 2011ዓ.ም በብሄራዊ ቤተ- ቤተ መዛግብት የፊልም ፌስቲቫል ይካሄዳል  ተብሏል።

ዓርብ የካቲት 22 ቀን 2011ዓ.ም በዓሉን በተመለከተ በጣይቱ ሆቴል የስነ-ጥበብ ድግስ መዘጋጀቱንም ጠቁመዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የፕረስ ሴክረታሪ ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ  ጨምረው እንደገለፁት በበዓሉ ዕለት ጠዋት  በጊዮርጊስ አደባባይ የተለመደው የዓድዋ ሰማዕታትን የማስታወስ እና የመዘከር ስነ-ስርዓት ይካሄዳል።

ያንን ተከትሎም በዓሉ ከሚደረግበት የጊዮርጊስ አደባባይ እስከ ዓድዋ ድልድይ የሚደረገው የእግር ጉዞ እና ዓርበኞችን እና የበዓሉ ታዳሚዎችን ግብር የማብላት ስነ-ስርዓትም በቅደም ተከተል እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የበዓሉ ቀን ከሰዓት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ አዘጋጅነት ሁሉም ዜና ያለክፍያ የሚታደምበት የ”አድዋ ፌስቲቫል!” የተሰኘ የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚቀርብም ተገልጿል።

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *