loading
አርትስ ዝክረ አድዋ “ፊታውራሪ ገበየሁ(አባ ጎራ)”

 

አርትስ ዝክረ አድዋ

“ፊታውራሪ ገበየሁ(አባ ጎራ)”

የመሀል ጦር አዛዡ  ፊታውራሪ ገበየሁ ከጣልያኖች ጋር በተደረጉ አውደ ውጊያዎች ሁሉ የተሳተፉ እና በሁሉም ጦርነት የተመሰከረላቸው ጀግና ነበሩ፡፡

የአምባላጌውን ምሽግ በመስበር  ጣሊያን መሸነፍ መጀመሩን ያሳዩ ፣በጣሊያን ላይ የመጀመሪያውን የድል ደውል ያሰሙ ጀግናም ናቸው፡፡

በወቅቱ የወጡ የፈረንሳይ ጋዜጦች ‹‹ኢትዮጵያዊው የአማባለጌ ጀግና ›› ሲሉ በፊት ገፆቻቸው አትመው እንደነበር  የተክለፃዲቅ መኩሪያ የታሪክ መፅሃፍ ይነግረናል፡፡

ፍት አውራሪ ገበየሁ የመቀሌውንም አውደ ውጊያ ተካፍለዋል፡፡ እንደውም በዚህ የመቀሌው ውጊያ እጃቸው ቆስሎ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታሪክ መዝግቧል፡፡

እኚህ ጀግና ታመውም ዱላ እየተመረኮዙ ጦርነቱን ተሳትፈዋል፡፡

ስለ ጀግንነታቸዉ እንዲህም ተዘፍኖላቸዋል፡፡

የንጉሥ ፊታውራሪ ያ ጎራው ገበየሁ
አላጌ በሩ ላይ ማልዶ ቢገጥማቸው
ለምሳም ሳይደርሱ ቁርሥ አደረጋቸው ተብሎ ፡፡

ፊታውራሪ ገበየሁ ገና ወደ አድዋ ሲዘምቱ እንዲህ ብለው ነበር፡-

‹‹ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ፣ እኔ እንደ አባቶቼ አይደለሁምናወግ አይገባኝም፤ ከፊት ለፊት ስፋለም ከወደቅሁ ግን እሬሳዬን  እትውልድ ቦታዬ ውሰዱልኝ››

የካቲት 23 ቀን 1888ዓ.ም ከጠዋቱ 11፡30 ላይ በተጀመረው የአድዋ ጦርነት ፊታውራሪ ገበየሁ የገጠሙት በእንዳ ኪዳነ ምህረት በኩል የመጣውን እና በጄኔራል አልበርቶኒ የሚመራውን የጣሊያን ጦር ነበር፡፡

ተክለፃዲቅ መኩሪያ  እንደፃፉት በጦርነቱ ፊታውራሪ ገበየሁ ከሰራዊቶቻቸው በመለየት ከቀኝ አዝማች ታፈሰ ጋር  ጎራዴያቸውን መዘው በዋናው የትግል አውድማ ተወርውረው ገቡ፡፡

በጎራዴያቸው  ሲፋለሙ ቆይተው ከርቀት በተተኮሰ ጥይት ተመተው ወደቁ፡፡ ሌሎችም መኮንኖች፣ ቀኝ አዝማቾች .ግራአዝማቾች እና ተዋጊዎች ሞተዋል፡፡

ያ ጎራው ገበየሁ ምን አሉ ምን አሉ
ያ ትንታግ ታፈሰ ምን አሉ ምን አሉ
እነ ደጃች ጫጫ ምን አሉ ምን አሉ
ተማምለው ነበር ከጦሩ ሲገቡ
አገሩን አቅንተው አድዋ ላይ ቀሩ፡፡ ተብሎ  ተገጠመ፡፡

አዲስ አበባ ድረስ ተማርኮ መጥቶ የነበረው የኢጣልያ መኰንን፣ጆቫኒ ቴዶኒ ስለ ፊታውራሪ  ገበየሁ በቢያን ኪኒና በማዘቶ ለሚመሩት መድፎች እየተመቱ አበሾች ወደ ኋላ ሲያፈገፍጉ አይቶ  ‹‹ፈሪ አንዴት ትሸሻላችሁ እኔ እንዴት እንደምሞት ለንጉሱ ሄዳችሁ ንገሩ›› በማለት ፈረሱን በአለንጋ አስነስቶ በሚዘንበው የመድፍ ጥይት መካከል ገባ፡ ሁሉም ስርሱን አይቶ ከመሃል ገቡ እና መድፈኞችን ማረኩ ሲል በማስታወሻው አስፍሯል፡፡

ክብር እና ሞገስ ለ ፊት አውራሪ ገበየሁ( አባ ጎራ)!

በሰላም ገብሩ ተዘጋጀ

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *