loading
8ኛው የህዳሴ ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል፡፡

8ኛው የህዳሴ ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል፡፡

የ8ኛ ዓመት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዓመታዊ የእግር ኳስ ውድድር በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሚሳተፉ 4 ክለቦች መካከል የሚደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ ይከናወናል፡፡

‹‹የታላቁ ህዳሴ ግድባችን መጠናቀቅ ብሄራዊ ኩራት ነው›› በሚል መሪ ሀሳብ በሚከናወነው በዚህ ውድድር ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማ በሚያደርጉት የርስበርስ ሁለት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም 9፡00 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ቡና፤ በ 11፡00 ሰዓት ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ ይጫወታሉ፡፡

በመጪው ዕሁድ የሁለቱ ጨዋታ አሸናፊዎች ለዋንጫ፤ ተሸናፊዎቹ ደግሞ ለደረጃ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

ውድድሩን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ም/ቤት ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰናድተውታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *