loading
ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዛሬ  በኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ ናቸው

የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከዛሬ  ጀምሮ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት  ጉብኝት ያደርጋሉ

የኬንያው ፕሬዝዳንት ክቡር ኡሁሩ ኬንያታ ከዛሬ  ጀምሮ በኢትዮጵያ ለሁለት ቀናት  የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በሁለቱ አገሮች መካከል ለዘመናት የቆየውንና በሁኔታዎች የማይለዋወጠውን ታሪካዊ ግንኙነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ኡሁሩ ኬንያታ የአፍሪካ አባት በመባል የሚታወቁት የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ የቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት  ጄሞ ኬንያታ ልጅ ሲሆኑ  ጄሞ ኬንያታ ከኢትዮጵያዊ ንጉሰ ነገሰት ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ እና ሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር የአፍሪካ አንድነት ደርጅት እንዲመሰረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ግንባር ቀደም መሪ ናቸው።

ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ለዘመናት የዘለቀውን ታሪካዊ ግንኙነት አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ።

በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ዓላማ አድርጎ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው የኢትዮ-ኬንያ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑም ተነግሯል።

በዚህ ፎረም ላይ ለመሳተፍም ቁጥራቸው 100 የሚደርሱ የኬንያ መንግስት ባለስልጣናት፣ የኮርፖሬት እና የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች ከፕሬዝዳንቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ ገብተዋል።

መረጃው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *