loading
ፖሊስ የዓድዋ ድል ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቅቄያለሁ አለ  

ፖሊስ የዓድዋ ድል ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነገ በአዲስ አበበ ከተማ የሚከበረውን የዓድዋ ክብረ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ማድረጉን በው ያስታወቀው።

በበዓሉ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንዳይከሰት ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ በቂ ዝግጅት ማደረጉንም ገልጿል፡፡

በበዓሉ ማንኛውም ዓይነት ሁከት በሚፈጥር አካል ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ልክ እንደወትሮው በዓሉ በሰላም ተጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግም ፖሊስ ጠይቋል፡፡

በዓሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነገ ምሽት 3 ሰዓት ድረስ በከተማዋ በተለያዩ ስፍራዎች በተለያዩ ዝግጅቶች  እንደሚከበር ታውቋል፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *