loading
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዚምባቡያዊያንን እንድረስላቸው እያለ ነው፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዚምባቡያዊያንን እንድረስላቸው እያለ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ከ17 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት የዚምባቡየ ዜጎች ከከባድ ድርቅ ጋር እየታገሉ እንደሚገኙ ድርጅቱ በሪፖርቱ አስታውቋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ከነዚህ መካካል ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

በድርቅ ለተገዱት ነዋሪዎች አስፈላጊውን ወጭ ለመሸፈን በትንሹ 234 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግም ድርጅቱ ይፋ አድርጓል፡፡

በሀገሪቱ በተከሰተው ድርቅሳቢያ በግብርና የሚተዳደሩ ዚምባቡያዊያን ሰብላቸው ምርት መስጠት ሳይችል በመቅረቱ ለእርዳታ እጃቸውን መዘርጋት ግድ ሆኖባቸዋል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *