loading
የቅንጬ አረም የሰሜን ወሎ ዞን አርሶ አደሮችን ህይወት እየተፈታተነ ነው

የቅንጬ አረም የሰሜን ወሎ ዞን አርሶ አደሮችን ህይወት እየተፈታተነ ነው

በሰሜን ወሎ ዞን ቆላማ ወረዳዎች አርሶአደሮች በአካባቢያቸው እየተስፋፋ የመጣው የቅንጨ አረም  የሰብልና የእንስሳት መኖን በማውደም ለችግር እየዳረጋቸው መሆኑን ተናገሩ።

ኢዜአ ያነጋገራቸው አርሶአደሮች ባለፉት 10 ዓመታት በእርሻ መሬታቸው ላይ የተከሰተው አረም በሰብል ምርታቸው ላይ ተጽዕኖ ፈጥሮብናል ብለዋል።

አርሶአደሮቹ እንዳሉት አረሙ ከእርሻ መሬታቸው ባለፈ የግጦሽ ቦታዎችን ወርሮ ሳሩን ሙሉ በሙሉ በማውደሙ እንስሳቱን ለረሀብ እየዳረጋቸው ነው ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እንስሳቱ በድርቅ ወቅት ሲመገቡት የወተቱን ጣዕም ይቀይረዋል ብለዋል።

የአካባቢው አርሶ አደር በየዓመቱ ጥረት ቢያደርግም የአረሙ ስርጭት ከአቅም በላይ በመሆኑ ማጥፋት እንዳልተቻለ የገለጹት አርሶአደሮቹ መንግስት ድጋፍ ያድርግልን ሲሉም ጠይቀዋል።

ኢዜአ የጠቀሰው የሰሜን ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ በዞኑ ራያቆቦ፣ ጉባላፍቶና ሀብሩ ወረዳዎች ብቻ 72 ሺህ ሄክታር መሬት በመጤ አረሙ መወረሩን አረጋግጧል። መጤ አረሙን ለማጥፋትም ፕሮጀክት ተቀርጾ ጥረት ቢደረግም መልሶ ስለሚተካ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አልተቻለም ነው ያለው መምሪያው፡፡

በቀጣዩ ወር አርሶ አደሩን መልሶ በማንቀሳቀስ በአረሙ የተወረረ 61 ሺህ ሄክታር መሬት ለማረም መታቀዱን መምሪያው ተናግሯል።

ጥናቶች እንደሚያረጋግጡት የቅንጨ መጤ አረም በነፋስ፣ በጎርፍ፣ በሰውና በእንስሳት እግር በፍጥነት የሚሰራጭ ሲሆን የሰብል ምርትን እስከ 65 ከመቶ ይቀንሳል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *