loading
የኤል ክላሲኮ ደርቢ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይከናወናል

የኤል ክላሲኮ ደርቢ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይከናወናል

 

 

የስፔን ላ ሊጋ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንት ተጀምረዋል፤ ጅሮና ራዮ ቫዬካኖን 2 ለ 0 ድል አድርጓል፡፡

 

ዛሬ ደግሞ ተጠባቂው የኤል ክላሲኮ የደርቢ ፍልሚያ ምሽት 4፡45 ላይ ሳንቲያጎ ቤርናቤው ላይ ሪያል ማድሪድ ከባርሴሎና ይገናኛሉ፡፡ ሁለቱ ቡድኖች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይህ የዛሬው የደርቢ ግጥሚያ ሶስተኛው ሲሆን ከቀናት በፊት ቤርናቤው ላይ የተካሄደውን የኮፓ ዴል ሬይ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ የካታላኑ ቡድን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

 

 

ዛሬ ደግሞ በሁሉም ውድድሮች ሁለቱ ቡድኖች 275ኛ የኤል ክላሲኮ የደርቢ ግንኙነታቸውን ያደርጋሉ፡፡ ልዩነት ፈጣሪው ሊዮኔል ሜሲ የምሽቱ ተጠባቂ ተጫዋች ነው፡፡

 

ከደርቢው ጨዋታ አስቀድሞ የሊጉ ሌሎች ጨዋታዎች ሲደረጉ ኢስፓኞል ከ ሪያል ሶሴዳድ፣ ቪያሪያል ከ ዲፖርቲቮ አላቬስ እና ሁሴካ ከ ሲቪያ ይጫወታሉ፡፡

 

የላ ሊጋውን የደረጃ ሰንጠራዥ ባርሳ በ57 ነጥቦች ይመራል፣ አትሌቲኮ ማድሪድ በ50 ነጥብ 2ኛ፣ ሪያል ማድሪድ በ48 ነጥብ 3ኛ እንዲሁም ሄታፌ በ39 ነጥብ 4ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *