loading
በቶክዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል

በቶክዮ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል

 


በጃፓኗ መዲና ቶክዮ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አድርገዋል፡፡

 


በሴቶች የተካሄደውን ውድድር ሩቲ አጋ በ2፡20፡40 አሸናፊ ስትሆን፤ ሄለን ቶላ በ2፡21፡01 ሁለተኛ እንዲሁም ሹሬ ደምሴ በ2፡21፡05 ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡ ኬንያዊቷ ፍሎረንስ ኪፕላጋት 4ኛ፣ በዳቱ ሂርጳ 5ኛ፣ አባብል የሻነህ 6ኛ በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡


በወንዶች የተደረገውን የሩጫ ውድድር ብርሃኑ ለገሰ በ2፡04፡48 ቀዳሚ ሲሆን፤ ኬንያዊው ቤዳን ካሮኪ በ2፡06፡48 ሁለተኛ፣ ሌላኛው ዲክሰን ቹምባ በ2፡08፡44 ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል፡፡

 


ምንጭ፡- አፍሪካን አትሌቲክስ ዩናይትድ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *