EthiopiaPolitics

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ኬንያ የሶስትዮሸ ውይይት አደረጉ

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ኬንያ የሶስትዮሸ ውይይት አደረጉ

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ኬንያ በሶስትዮሽ ግንኙነት ላይ ተወያዩ።

የሶስቱ ሃገራት መሪዎች በቀጠናው ኢኮኖሚያዊ ውህደት ማምጣት በሚቻልባችው ጉዳዮች እና በሚስተዋሉ ወቅታዊ ጉዳች ዙሪያ መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አስመራን ጎብኝተዋል።

አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
መሪዎቹ በኤርትራ በነበራቸዉ ጉብኝት በሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ተቋማትን ተመልክተዋል።

የተለያዩ ግድቦችን፣ የጸሀይ  የኤልክትሪክ ሀይል ማመንጫ ማእከልን እና የከብት እርባታ ጣቢያም የጉብኝታቸዉ አካል ነበሩ፡፡

የሶስትዮሽ ዉይይት ዶክተር አብይ ስልጣን ከያዙ በኋላ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን ግንኙነት ለማጠናከር የሚሰሩዋቸዉ ስራዎች አንዱ አካል ነዉ ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button