loading
አፍሪካን አርቲስት ፒስ ኢኒሼቲቭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይንና ፕሬዝዳንት ኢሳያስን ልሸልም ነዉ አለ፡፡

አፍሪካን አርቲስት ፒስ ኢኒሼቲቭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይንና ፕሬዝዳንት ኢሳያስን ልሸልም ነዉ አለ፡፡

አፍሪካን አርቲስት  ፒስ ኢኒሼቲቭ የተሰኘ በአፍሪካ ህብረት ስር ያለ አንድ የሽልማት ድርጅት  ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን ልሸልም ነው አለ፡፡

ተቋሙ መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰላም እንዲሰፍን እና የህዝብለህዝብ ትስስሩ ዳግም እንዲመለስ ላበረከቱት አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት ሲል የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 30/2011 ዓ.ም ሽልማቱን እንደሚያበረክት በኢትዮጵያ የአፍሪካን አርቲስት ፒስ ኢኒሼቲቭ        አስተባባሪ አቶ አብይ ሽመልስ ገልፀዋል፡፡

ከ5 አመታት በፊት በ28ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የተቋቋመው እንቅስቃሴው በአህጉር ደረጃ አርቲስቶች እና ኪነጥበብ ላይ ያሉ ባለሞያዎችን በማስተባበር ለሰላም መስፈን የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የሚያስተባብር እንቅስቃሴ እንደሆነም ሰምተናል፡፡

በመሆኑም የእውቅና ሽልምቱን ላለፉት አራት አመታት በአህጉሪቱ ለሰላም እና መረጋጋት የሚበረታታ ስራ ለሰሩ አካላት ሲሰጥ መቆየቱን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

ለዋቢነትም በአፍሪካ ሀብረት ለሴቶች ሰላም እና መረጋጋት  ላይ አስተዋፅኦ ያደረጉትን ማደም ቤኒታዲዮችን መሸለሙ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *