Politics

አሜሪካ ከፍልስጤም ጋር  የሚያገናኛትን ቆንስላ ፅህፈት ቤት ዘጋች፡፡

አሜሪካ ከፍልስጤም ጋር  የሚያገናኛትን ቆንስላ ፅህፈት ቤት ዘጋች፡፡

ዋሽንግተን ከፍልስጤም ጋር በዲፕሎማሲ የምትገናኝበትን የቆንስላ ፅህፈት ቤቷን ዘግታ በእስራኤል የአሜሪካ ኢምባሲ ስር እንዲጠቃለል አድርጋለች፡፡

በድርጊቱ የተበሳጩት የፍልስጤም ባለ ስልጣኖች ነገሩን ቀድሞውንም ታሞ የነበረውን ግንኙነት ገደሉት በማለት የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን አስተዳደር ወቅሰዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው አሜሪካ ኢየሩሳሌም የእስራኤል ዋና ከተማ ትሁን ብላ እውቅና ከሰጠች ጀምሮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ህጋዊ ግንኙነት ተቋርጧል፡፡

አሜሪካ ግን በኢየሩሳሌም፣ በዌስት ባንክ እና በጋዛ ሰርጥ ከቀድሞው የተለወጠ የፖሊሲ ለውጥ  የለም የሚል መግለጫ ነው የተሰጠችው፡፡

ቆንስላ ፅህፈት ቤቱ የመዘጋቱ ነገር ባለፈው ጥቅምት ወር በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ በኩል ይፋ ሲደረግ ፍልስጤማዊያንን በእጅጉ አስቆጥቶ ነበር፡፡

አሜሪካ ለፍልስጤም ይሰጥ የነበረውን በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የሰብዓዊ እርዳታ ገንዘብ ያቋረጠች ሲሆን በምክንያትነት ያነሳችውም የፍልስጤም አስተዳደር ለሰላም ድርድር ቸልተኝነት አብዝቷል የሚል ነው፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button