loading
አውስትራሊያ አዲስ አበባ የጀመረችውን የጎዳና ላይ ልጆችን በዘላቂነት የማቋቋም ፕሮጀክት እደግፋለሁ አለች፡፡

 

አውስትራሊያ አዲስ አበባ የጀመረችውን የጎዳና ላይ ልጆችን በዘላቂነት የማቋቋም ፕሮጀክት እደግፋለሁ አለች፡፡

አውስትራሊያ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ግብረሰናይ ድርጅቶቿ  በኩልም አዲስ አበባ የጀመረችውን የጎዳና ላይ ልጆችን በዘላቂነት የማቋቋም ፕሮጀክት እንደምትደግፍ

በአምባሳደሯ በኩል ተናግራለች፡፡

አዉስትራልያ ድጋፍዋን የገለጸችዉ የአዲስ አበባ ከተማ  ምክትል ከንቲባ  ታከለ ኡማ ከአውስትራሊያ አምባሳደር ሚስተር ፒተር ዶይሌ ጋር በፅህፈት ቤታቸው በተወያዩበት ወቅት ነዉ፡፡

የአውስትራሊያው አምባሳደር ሃገራቸው ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ መንገድ እንደምትደግፍ እና አስፈላጊውን ድጋፍ በሙሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም ሚስተር ፒተር ዶይሌ ሃገራቸው ሸገርን ለማስዋብ የተጀመረውን ፕሮጀክት በምትደግፍበት ሁኔታ ላይ ከኢኒጀነር ታከለ ኡማ ጋር ተወያይተዋል፡፡

መረጃውን ያገኝነው ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *