loading
የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሎምፒክ ቡድን መጋቢት 1 ከዩጋንዳ ጋር ይጫወታል ተባለ

የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሎምፒክ ቡድን መጋቢት 1 ከዩጋንዳ ጋር ይጫወታል ተባለ

እ.አ.አ በ2020 በጃፓን ዋና ቶክዮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር፤ በሴቶች ኦሎምፒክ እግር ኳስ ውድድር የአፍሪካ ዞን የዙሩ የቅድመ ማጣሪያ ውድድር፤ ኢትዮጵያ ከ ዩጋንዳ መጋቢት 25/2011 ዓ/ም በአዲስ አበባ ስታዲየም የምትጨወት መሆኑን የአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል /ፊፋ/ አስታውቆኛል ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በይፋዊ ድረ ገፁ መረጃውን አስፍሯል፡፡

ጨዋታውን ግብፃውያን ዳኞች እና ጅቡቲያዊ የጨዋታ አሰሰር እንዲሁም ናጀሪያዊ ኮሚሽነር  እንደሚመሩት ተጠቁሟል፡፡

የመልሱ ግጥሚያ ከሶስት ቀናት በኋላ መጋቢት 28/2011 ዓ/ም በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ ስታርታይምስ ስታዲየም እንደሚካሄድ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *