loading
በቻይና በሚካሄደው አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሙያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተባለ

በቻይና በሚካሄደው አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ኢትዮጵያውያን የፈጠራ ባለሙያዎች ተሳታፊ ይሆናሉ ተባለ።

 

‘ሁዋዌ’ የተሰኘው ተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች ባዘጋጀውና ለሶስት ወራት በቆየው የቴክኖሎጂ  ውድድር  ከፍተኛ ዉጤት ያመጡ  ስድስት ተማሪዎችና አንድ መምህር እዉቅናና ሽልማት የተሰጣቸው መሆኑም ተነግሯል።

ከነዚህ መካከል የላቀ ውጤት ያመጡት ይብራህ መሀሪ እና ያሬድ ረዳ የተባሉት አሸናፊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃገራቸውን ወክለው ቻይና በሚደረገዉ አለም ዓቀፍ የመገናኛ ኢፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዉድድር ላይ ለመሳተፍ ወደዚያው እንደሚጓዙ ይፋ ተደርጓል።

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና የኔትወርክ ዳይሬክተር አቶ ዘላለም  አሰፋ  እንደተናገሩት በአገሪቱ ያለዉ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ  እንዲያድግ ለማድረግ ተማሪዎች ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ካለው ተቋም ጋር እንዲሰሩ ይደረጋል ።

ተማሪዎችን ተግባር ተኮር የሆነ ትምህርት በማስተማር አለም ዓቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና መሰራት እንዳለበትም ጠቁመዋል። መረጃውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገፅ የተገኘ ነው፡፡

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *