loading
በኢትዮጵያ ዘላቂ የከተሞች ዕድገት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ ዘላቂ የከተሞች ዕድገት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።

ጥራት ያለው የትምህርት ስርዓትን ለማስፈን አለማቀፍ ተሞክሮና ትብብር ያስፈልጋል ተብሏል።

በአሜሪካ መንግስት በተዘጋጀውና በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚሁ አውደጥናት ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያም እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በመማር ማስተማር፣ በምርምርና በማህበራዊ አገልግሎት ዙሪያ ጥራት ያለው ተግባር ለማከናወን ዓለም ዓቀፍ ትብብርና ተሞክሮን ማጠናከር ያስፈልጋታል።

የአሜሪካ መንግስት የአገሪቱን የትምህርት ስርዓት ለመደገፍና  አለም ዓቀፋዊ ትብብርን ለማሳደግ እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ በዘርፉ  የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ጠቃሚ ነው ሲሉም ዶክተር ሂሩት ተናግረዋል።

ውይይቱ አገሪቱ አዲሱን የትምህርት ፍኖተ ካርታ እያዘጋጀት ባለችበት ወቅት መከናወኑ ዓለም ዓቀፋዊ ይዘት ያለው ተሞክሮን በፍኖተ ካርታው ለማካተት መልካም አጋጣሚ ይሆንላታል ብለዋል ዶክተር ሂሩት።

‘’በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዓለም አቀፋዊነትና የአቅም ግንባታ’’ በሚል ርዕስ እየተካሄደ የሚገኘው ይኸው አውደጥናት የትምህርት ይዘትንና ተቋማትን ጥራት ማሳደግ፣ የአቅም ግንባታን ማጎልበትና አለም ዓቀፋዊ አስተሳሰብ እና ተሞክሮዎችን ለማስፋት ያለመ ነው ተብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *