loading
መጣል የጀመረው ዝናብ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ እንደሚቀጥል ሚትዩሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ

አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የበልግ አብቃይ አካባቢዎች መጣል የጀመረው ዝናብ ከቀን ወደ ቀን እየተጠናከረ እንደሚቀጥል የብሔራዊ ሚትዩሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።

 

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚቀጥለው አንድ ወር ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ይኖራቸዋል ብሏል።

 

በኤጄንሲው የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አህመዲን አብዱልከሪም  እንደተናገሩት በኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ የአርሲና የባሌ ከፍተኛ ቦታዎች እንዲሁም የቦረናና የጉጂ ዞኖች ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ያገኛሉ ከተባሉት መካከል ናቸው፡፡

አቶ አህመዲን እንዳሉት በአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደርም ዝናቡ ተጠናክሮ የሚቀጥልባቸው አካባቢዎች ይሆናሉ፡፡

ጋምቤላ፣ ምስራቅና ደቡብ ትግራይ ዞን፣ እንዲሁም በደቡብ ክልል የተለያዩ በልግ አብቃይ ዞኖች በመጭው አንድ ወር በቂ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ተገምቷል እንደኤጀንሲው ገለጻ ፡፡የአዲስ አበባ ዝናብ አሁን ባለበት መልኩ ለአንድ ሳምነት ይቀጥላል ነው የተባለው።

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *