EthiopiaPolitics

ሳምንቱ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የዲፕሎማሲ  ስኬት ያስመዘገበችበት ነው ተባለ፡፡

ሳምንቱ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ የዲፕሎማሲ  ስኬት ያስመዘገበችበት ነው ተባለ፡፡

በሳምንቱ ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በምስራቅ አፍሪካ  በሰሩት ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራ በክልሉ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት በማስፈን ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ውህደት ለመመስረት የሚያስችሉ የሁለትዮሸ እና የሶሰትዮሽ ስኬታማ ውይይቶች እንዲካሄድ አድርገዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በኬንያ፣ በሶማሊያ አና በደቡብ ሱዳን አገሮቸ መሪዎቸ መካከል የሶስትዮሽ እና በርካታ የሁለትዮሽ ውይይቶች እንዲደረጉ ድልድይ ነበረች፡፡ ዉጤታማም ነበሩ፡፡

የኬንያ ፕሬዝዳንት  አሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ያደረጉት የሁለትየሽ ውይይት በሳምንቱ ለተገኘው የዲፕሎማሲ ስኬት እንደ ፋና ወጊ የሚቆጠር ነው ተብሏል።

ሶስቱ መሪዎቸ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ ኢሳያስ አፈወርቂ እና ፕሬዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት በጁባ በመገናኘት የሁለትዮሽ እና የሶስትዮሽ ተመሳሳይ ውይይቶችን አድርገዋል።

በዚሁ ውይይት መሪዎቹ ያላቸውን ልዩነት ወደ ጎን በመተው በጋራ ጉዳዮቸ ላይ ህዝባችውን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስቸሉ ተመሳሳይ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት  መሁመድ አብዱላሂ መሀመድ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከዶክተር አብይ አህመድ ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል፡፡

በቀጣይም ወደ ናይሮቢ በማቅናት ፕሬዝዳንት አሁሩ ኬንያታ እና ፕሬዝዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ሙሀመድ በናይሮቢ በመገናኘት በክልሉ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን በሚቻልባቸው ጉዳዮች እና ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ውህደት ለማምጣት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተመሳሳይ የሁለትዮሽ እና የሶስትዮሽ ውይይቶችን አድርገው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል።

ባጠቃላይ ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት እንደተገኘዉ መረጃ  ኢትዮጵያ ባካሄደችዉ ሽምግልና በሶማሊያ እና በኬንያ መካከል ከባህር ወሰን ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ የነበረው ከፍተኛ አለመግባባትና ውጥረት በድርድርና በስምምነት እንዲፈታ ሁለቱን አገሮች ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

 

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button