loading
IAAF 5,000 ሜትርን ከ2020 ዲያመንድ ሊግ ጀምሮ አሰናብታለሁ አለ

IAAF 5,000 ሜትርን ከ2020 ዲያመንድ ሊግ ጀምሮ አሰናብታለሁ አለ

የአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) እ.አ.አ. ከ2020 ዓ/ም የዲያመንድ ሊግ ውድድር ጀምሮ፤ የ5,000 ሜትር የሩጫ ውድድር ከዲያመንድ ሊግ መሰረዙን በድረ ገፁ አስታውቋል፡፡

ማህበሩ ይህን ውሳኔ ያሳለፈው ዲያመንድ ሊግ የ10ኛ ዓመት የምስረታ ዘመኑን እያከበረ ባለበት ወቅት ሲሆን የአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ዲያመንድ ሊግ ቦርድ እና ዳይሬክተሮች ውድድሩን የተሻለ ለማድረግ ከ2020 ጀምሮ የተለያዩ ማሻሻያዎች ላይ ውይይት ሲያደርግ ነው፡፡

በዲያመንድ ሊግ በሁለቱም ፆታዎች 24 ዲሲፕሊኖች ሲኖሩ ከዚህ በፊት የነበረው 32 የውድድር አይነቶች ታጥፈው በአጠቃላይ በወንድና በሴት 12 የውድድር አይነቶች ብቻ እንደሚኖሩ፤ ረዥሙ የሩጫ ርቀትም 3,000 ሜ ብቻ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡

በ5 ሺ ሜትር ኢትዮጵያዊያን እና የጎረቤት ኬንያ አትሌቶች የነገሱበት እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በዘንድሮው የዲያመንድ ሊግ (2019) ውድድር በአፍሪካ፣ ኤስያ፣ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና አሜሪካ የሚገኙ 14 የውድድር ስፍራዎች፤ ከ83 ሀገራት የተወጣጡ 789 አትሌቶች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *