loading
በቻምፒዮንስ ሊግ ዩቬንቱስ የመጀመሪያውን የ2 ለ 0 ሽንፈት ቀልብሶ አለፈ

በቻምፒዮንስ ሊግ ዩቬንቱስ የመጀመሪያውን የ2 ለ 0 ሽንፈት ቀልብሶ አለፈ
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የማጣሪያ ግጥሚያዎች ትናንት ምሽት ሲካሄዱ አሁንም አስገራሚ ውጤቶች መመዝገባቸውን ቀጥለዋል፡፡
የጣሊያኑ ዩቬንቱስ እና የስፔኑ አትሌቲኮ ዴ ማድሪድ ያደረጉት ጨዋታ፤ በገጉት የተጠበቀ ሲሆን የመጀመሪያው ግጥሚያ ደግሞ በአትሌቲ 2 ለ 0 ድል አድራጊነት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፉን ግምት ለአትሌቲኮ እንዲሰጥ አድርጎት ነበር፡፡
ይሁን እንጂ በምሽቱ በአሊያንዝ ስታዲየም የተደረገውን ግጥሚያ አሮጊቷ በፖርቱጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሶስት ጎሎች ታግዛ 3 ለ 0 በመርታት ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች፡፡ ሮናልዶ በቻምፒዮንስ ሊግ ታሪክ 124ኛ ጎሉ ላይ ሲደርስ፤ በምሽቱ ሁለቱን በጨዋታ አንዱን በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሮ ቡድኑ በድምር ውጤት 3 ለ 2 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር መዋሀድ ችሏል፡፡
ሌላኛው በተመሳሳይ ሰዓት የተደረገው ጨዋታ ደግሞ ማንችስተር ሲቲ ኢቲሃድ ላይ ሻልከን 7 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ረምርሞታል፡፡ በአጠቃላይ ውጤት ደግሞ 10 ለ 2 ሩብ ፍፃሜውን የጠቀላቀለ ሶስተኛው የእንግሊዝ ቡድን ሁኗል፡፡
ለሲቲ የድል ጎሎቹን ኩን አጉዌሮ 2×፣ ሊሮይ ሳኔ፣ ራሂም ስተርሊንግ፣ በርናርዶ ሲልቫ፣ ፊል ፎደን እና ጋብሪየል ጀሱስ ከመረብ አገናኝተዋል፡፡
ትናንት ምሽት ዩቬንቱስ እና ማንችስተር ሲቲ ወደ ተከታዩ ዙር ማለፋቸውን ተከትሎ፤ ሩብ ፍፃሜው ላይ የደረሱክለቦች ስድስት የደረሱ ሲሆን ከዚህ በፊት ቶተንሃም፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ አያክስና ፖርቶ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል፡፡
ዛሬ ምሽት 5፡00 በተመሳሳይ ሰዓት ባየርን ሙኒክ ከ ሊቨርፑል አሊያንዝ አሬና ላይ እና ባርሴሎና ከሊዮን በካምፕኑ ይጫወታሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *