Uncategorized

ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባለው ምቹ የኢንቨስትመነት አማራጭ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበላቸው

ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ባለው ምቹ የኢንቨስትመነት አማራጭ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበላቸው።

በቻይና ሻንሃይ ከተማ የጨርቃርቅ ገቢና ወጪ ንግድ ማህበር አዘጋጅነት የምስራቅ አፍሪካ የኢንቨስትመንት ሴሚናር ተካሂዷል። ኢትዮጵያም የኢንቨስትመንት ሴሚናሩ ላይ የኢትዮጵያ ልዑክ ተሳታፊ ሆኗል።

በሴሚናሩ ላይ በቻይና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ተሾመ ቶጋን ጨምሮ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ እና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ ኢትዮጵያን ወክለው ተሳትፈዋል።

በሴሚናሩ ላይ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሁሉን አቀፍ ለውጥ በመግለጽ፣ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ባለው ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲሳተፉ ጥሪ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን የቢዝነስ ስራ ለማቀላጠፍ የሚያስችልና በጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቅርብ ክትትልና ድጋፍ የሚደረግለት ኮሚቴ ተቋቁሞ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በንግግራቸው ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በአቶ አበበ አበባየሁ እና በሌሊሴ ነሜ በኩል በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን በተመለከተ ገለጻና ማብራሪያ ተደርጓል  ሲል የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ገልፃል።

ከገለጻው በኋላም በርካታ የቻይና ታዋቂ ኩባንያ ሃላፊዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንት በስፋት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እና አዳዲሶችም በስፋት ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳደረባቸው በነበረው የሁለትዮሽ ውይይት መግለጻቸውን ለመገንዘብ ተችሏል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button