loading
አዲሱ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ለፖለቲካ እስረኞች ይቅርታ አደረጉ፡፡

አዲሱ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ለፖለቲካ እስረኞች ይቅርታ አደረጉ፡፡

በቅርቡ ጆሴፍ ካቢላን ተክተው የፕሬዝዳንቱን ስልጣን በምርጫ የተረከቡት ፊሊክስ ሺሴኬዲ 700 የሚሆኑ የፖለቲካ እስረኞች ከእስር እንዲለቀቁ አድርገዋል፡፡

ሺሴኬዲ ስራቸውን የጀመሩበትን አንድ መቶኛ ቀናት ምክንያት በማድረግ ነው እስረኞቹ በይቅርታ እንዲፈቱ በፊርማቸው የፈቀዱት፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ካቢላ እነዚህን ፖለቲከኞች የሀገሪቱ የደህንነት ስጋቶች ናቸው በማለት ነበር ያሰሯቸው፡፡

ሺሴኬዲ በሀገራችን ለዘመናት የተጓደለውን ፍትህ ለማስፈን ጠንክረን እንሰራለን ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡

በፖለቲካ አመለካከታቸው በሚደርስባቸው ወከባ እና እንግልት ዲሞክራቲክ ኮንጎን ጥለው የተሰደዱት ሁሉ ወደ  ሀገራቸው እንዲመለሱም ሁኔታዎችን እናመቻቻለን ብለዋል፡፡

ስልጣን በያዙ በጥቂት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉዟቸውን ወደ ጎረቤት ሪፓብሊክ ኮንጎ ባደረጉበት ወቅት በዚያ ለሚገኙ የፖለቲካ ስደተኞች ሀገራችሁ አጥብቃ ትፈልጋችኋች ኑ እና በጋራ እናሳድጋት የሚል መልእክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *